ፎቶ መቃኛ የስልክዎን ካሜራ በመጠቀም ተወዳጅ የታተሙ ፎቶዎችዎን እንዲቃኙ እና እንዲያስቀምጡ የሚያስችልዎት የGoogle ፎቶዎች ቃኚ መተግበሪያ ነው።
እንከን የለሽ ፎቶ እና ከነጸብራቅ ነጻ
የፎቶን ፎቶ ብቻ አያንሱ። ፎቶዎችዎ የትም ቢሆኑ፣ የተሻሻሉ ዲጂታል ቅኝቶችን ይፍጠሩ።
– ቀላል በሆነ የደረጃ-በ-ደረጃ የቀረጻ ፍሰት ከነጸብራቅ-ነጻ ቅኝቶችን ያግኙ
– ጠርዝ ማወቅን መሰረት ያደረገ ራስ ሰር ክርከማ
– ቀጥተኛ፣ ባለ አራት ጎን ቅኝቶች ከየአተያየት እርማት
– ብልህ ማዞር፣ በየትኛውም መንገድ ቃኟቸው ፎቶዎችዎ የቀኝ-ጎን-ወደላይ ሆነው ይቆያሉ
በሰከንዶች ውስጥ ይቃኙ
አርትዖት ላይ አነስ ያለ ጊዜ እንዲሁም መጥፎ የልጅነት የፀጉር ቁርጥዎን መመልከት ላይ የበለጠ ጊዜ እንዲያጠፉ ተወዳጅ የታተሙ ፎቶዎችዎን በፍጥነት እና በቀላሉ ይቅረጹ።
በGoogle ፎቶዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተፈልጎ የሚገኝ
ቅኝቶችዎን ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ተፈልገው የሚገኙ እና የተደራጁ ሆነው እንዲቆዩ በየGoogle ፎቶዎች መተግበሪያው ምትኬ ያስቀምጡላቸው። በፊልሞች፣ በማጣሪያዎች እና በየላቁ የአርትዖት መቆጣጠሪያዎች ቅኝቶችዎን ህይወት ይዝሩባቸው። እናም አገናኝ በመላክ ብቻ ከማንኛውም ሰው ጋር ያጋሯቸው።